1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ የተሰጠ ቡራኬና የአፍሪቃዉያን አስተያየት

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 13 2016

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ ቤተክርስትያኒቱ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መቀበል እንደምትፈልግ እና ቡራኬ እንዲሰጥ መደንገጋቸዉ ግርታን ፈጥሯል። የፍንሲስ ይህ እርምጃ በአፍሪቃዉያን ዘንድ ግራ መጋባትን አስከትሏል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች በ,ኩላቸዉ የበለጠ እንዲደረግ ጠይቀዋል። አፍሪቃዉያን በአብዛኛዉ በጾታዊ ጉዳይ ጠንካራ አመለካከት አላቸው።

https://p.dw.com/p/4aVjX
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስምስል GUGLIELMO MANGIAPANE/REUTERS

አሳዛኙ ነገር የቫቲካን መግለጫ በምዕራባውያን ሚዲያዎች ተጠልፎ የፈለጉትን መርጠው ለጥፈዉታል።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትኛዉም አይነት የተመሳሳይ ጾታ  አፍቃሪዎችን መቀበል እንደምትፈልግ በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ ይፋ ማድረጓ ብዙ ግርታን ፈጥሯል። የሮማሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ የሰጡት በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ እለት ነዉ። የቤተክርስትያኗ ይህ እርምጃ በአፍሪቃዉያን ዘንድ ግራ መጋባትን አስከትሏል። በሌላ በኩል የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የበለጠ እንዲደረግ መፈለጋቸዉን ማስታወቃቸዉ ተዘግቧል። የዶቼ ቬለዉ አይዛክ ካሌጂ ከጋና እንደጻፈዉ፤ በአፍሪቃ ግብረ ሰዶማዊነት አወዛጋቢ ርዕስ ነው። በአህጉሪቱ የሚገኙ አብዛኞቹ ነዋሪዎች በጾታዊ ዝንባሌ ላይ ጠንካራ እና በጣም ወግ አጥባቂ አመለካከት አላቸው።

 አፍሪቃ ግብረ ሰዶምን መቀበል አትችልም

 ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት ይችላሉ ብለዉ ማፅደቃቸው ብዙ አፍሪቃውያንን ግራ አጋብቷል ፤ ሁኔታዉ የተደበላለቁ ስሜቶች እንዲፈጠሩም አድርጓል። ደቡብ አፍሪቃዊዉ ሜሪ ሌሴባ ለዶቼ ቬለ እንደተናገረዉ ተግባሩ አሳፋሪ ነዉ። “እንደ ክርስቲያን በጣም አፍሬያለሁ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያደረጉት ያሳፍራል። እሳቸዉ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ላይ ተጠምደዉ እና አጽድቀዉ ክርስቲያን ነኝ ይላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ፈጠረ ይላል  እንጂ  አዳምንና ስቴፈንን ፈጠረ አይልም። »

ዜናዉን የሰሙ አያህ አለን ብራቮ የተባሉት ሌላዉ ካሜሩናዊ ተመሳሳይ አስተያየት ነዉ የሰጡት። ካሜሩናዊዉ የሊቃነ ጳጳሳቱ ዉሳኔ ለኔ ምንም ማለት አይደለም ፤ እንደዉም ሃይማኖትን እንድጠራጠር እያደረገኝ ነዉ። እምነቴን ለማጣት እየሞከርኩ ነዉ ሲሉ ተናግሯል። ደቡብ አፍሪቃ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃርያን በአንጻራዊ ምቹ የሆነች ብቸኛዋ አፍሪቃዊት ሃገር ናት። የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ህጋዊ የሆነባት ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገርም ናት።  ሆኖም ግን ከፍተኛ የሆነ የግብረ-ሰዶማውያን ጥላቻ ጥቃቶችም የሚታዩባት የሚከሰቱባት ሃገርም ነች።

የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አስተያየት

በጆሃንስበርግ የምትኖረዉ ቴምቢ ሲንዳኒ ለዶቼ ቬለ እንደተናገረችዉ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ውሳኔ ተገቢ እና የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ማህበረሰብን ደህንነት የሚጠቅም ነው። «ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያደረጉት ነገር በጣም የተከበረ እና በጣም ጥሩ እርምጃ ነዉ።  እሳቸዉ ያደረጉት ክርስቲያን፣ ግብረ ሰዶማውያን  ኅብረተሰቡ ሳያብጠለጥላቸዉ እንዲቀርቡ  ነዉ የፈቀዱት።» ቴምቢ ሲንዳኒ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ዉሳኔያቸዉ ደግነትን ነዉ ያሳዩት ስትልም አክላለች።  እንዲህ ያለው ጠንካራ ምላሽ፤ ከደቡብ አፍሪቃዊቷ ማላዊ አገር የመጡትን አጥባቂ የካቶሊክ እምነት ተከታይ እና የሃይማኖት ተንታኝ ፍራንሲስ ምፔካንሳምቦን እጅግ አሳስቧቸዋል፤ አስቆጥቷቸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠታቸዉ ውዥንብር ፈጥሯል፤ ምክንያቱም ለግብረ ሰዶማዊነት ፈቃድ እየሰጠ ነው ተብሎ በተሳሳተ መንገድ እየተተረጎመ ነው ባይ ናቸዉ።  

ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች
ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችምስል Manish Swarup/AP/picture alliance

የአፍሪቃ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያን ምላሽ

“በአፍሪቃ የምትገኘዉ ቤተ ክርስቲያን ለዜናው የሰጠችዉ ምላሽ የተለያየ እና በተወሰነ መልኩ ግራ በተጋባ መልኩ ነው። እንደባህላችን አፍሪቃ ግብረ ሰዶምን መቀበል አይችልም። አሳዛኙ ነገር የቫቲካን መግለጫ በምዕራባውያን ሚዲያዎች ተጠልፎ የፈለጉትን መርጠው ለጥፈዉታል። ምክንያቱም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው አስረግጠዉ እንደተናገሩት  የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን መቀበል አትችልም ብለዉ አረጋግጠዋል።» ፀረ- ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ መብቶች እና ህጎች በተደነገጉበት በአብዛኛዉ የአፍሪቃ ሃገራት  ውስጥ፣ የተሰማዉ ይህ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ ይከወናል ማለት እንዳልሆነ ይሰማቸዋል።  የሮማ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ ባለፈዉ ሰኞ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ ሲሰጡ እንዳሉት የቤተ-ክርስትያኒቱ ቄሶች የተመሳሳይ ፆታ  ያልተለመዱ  ጥንዶችን በአንዳንድ ሁኔታዎች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቅጃለሁ።   ጆሃንስበርግ የምትኖረዉ የተመሳይ ጾታ አፍቃሪ ቴምቢ ሲንዳኒ ፤ እንደተናገረችዉ ይህ የሊቃነ ጳጳሱ የቡራኬ ዉሳኔ ፤ እንደ ትንሽ ድል ነው የሚሰማኝ። ስለ ማንነታችን በግልፅ የምንቆምበት እና የምንወደድበት ጊዜም ይመጣል የሚል  ተስፋን ይሰጠኛልም።

አይዛክ ካሌጂ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ