1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉማ ሽልማት አዘጋጅ እስር

ቅዳሜ፣ ሰኔ 3 2015

የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጇ ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ) ከዚህ ምስል ጋር በተያያዘ ዛሬ እረፋዱን የእስር ማዘዣ ወጥቶባታል ተብሎዋል።

https://p.dw.com/p/4SQMC
 Ethiopia / Addis Ababa 10.06.2023
ምስል Hana Demissie/DW

የጉማ ሽልማት አዘጋጅ እስር

የጉማ አዋርድ አዘጋጅ በፖሊ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ተሰማ።  ለፊልም ሽልማት አዘጋጅ መታሰር  ምክን ያት ሳይሆን እንዳልቀረ የተነገረው ሚካፕ የተሰራችው  የቴሊቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅዋ በማህበራዊ ሚዲያው  "ልጅ ማኛ" በሚል መጠሪያ  የምትታወቀው እጩ ዶ/ር ፍላጎት አብርሀም በሥነስርዓቱ አፏን ሸብባና ግንባሯን በጥይት እንደተመታ ሰው በሜክአፕ ተሰርታ መቅረቧ ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነው። ፍላጎት አብርሃም የእስር ማዘዣ እንደወጣባትም ለማወቅ ተችሏል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ጥበበኞች በመሸለም የሚታወቀው ጉማ አዋርድ ሰኔ 02/10/2015  አመተምህረት  በርካታ የሙያው ታዳሚዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊልም ሽልማት ስነስራእቱ ተካሄድዋል ። ትላንት ለ 9ኛ ግዜ የተካሄደው የ "ጉማ አዋርድ"ን ያዘጋጀው   ዮናስ ብርሃነ መዋ በዚሁ  ምሽት  ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጉዋል።

በእለቱ ከሽልማቱ በኋላ በነበረው ዝግጅት ከቤተሰቦቹ ጋር የነበረው ዮናስ እኩለ ሌሊት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከባለቤቱ ጋር ተይዘው የነበረ ሲሆን  ። ባለቤቱን ለቀው  አዘጋጂን ዪናስ ብርሀነ መዋ  ምሽቱን  በአዲስ አበባ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ ባለ ፓሊስ ጣቢያ ማደሩን ለማወቅ ተችሏል።

ትላንት ምሽት ከስካይ ላይት ሆቴል ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከበቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ   የተወሰዱት  አቶ ዮናስ ብርሀነ መዋ ዛሬ ረፋዱን  አዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ቦሌ ምድብ ፍርድ ቤት ቀርበዋል ፖሊስ አቶ ዮናስ  ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ አሁን በአካል ፍርድቤት ካልቀረቡ ግለሰብ ጋር በመሆ  ህዝብን በመንግስት ላይ  የሚያስነሳ የፖለቲካ  ስራ ሰርተዋል የሚል ክስ በማቅረብ  ለምርመራ 14 ቀን ቀጠሮ ጥይቆባቸውዋል።

ጉዳዪን የተመለከተው  የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  አቶ ዮናስ የቀረበባቸው ክስ ዋስትና የማያስከለላቸው በምሆኑ  የቦሌ ክፍለከተማ መምሪያ ፖሊስ የ ጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ውድቅ በመድረግ በመታወቂያ እና በ 5 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ብይን ቢሰጥም  በፊዲራል ፖሊስ ፒያሳ ወደሚገኘው  የማእከላዊ  እስርቤት እንደተውሰዱ  ለማውቅ ችለናል።

ለአመታዊው ሀገር አእቀፍ የፊልም ሽልማት  አዘጋጅ መታሰር  ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ የተነገረው አልባስት በቴሊቪዥን አዘጋጅዋ በማህበራዊ ሚዲያው  "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው እጩ ዶ/ር ፍላጎት አብርሀም ነጭ የሙሽራልብስ ተላብሳ  ግንባዋ በጥይት የተመታ አፍዋ በሽቦ  የተሸበበች ሴት በመምሰል በሜካፕ በመሰራት  የቀረበችበት ጉዳይ እንደሆነ እየተነገረ ነው።  ሌሎች አርቲስቶችም የሴቶችን አስገድዶ መደፈር እና ድብደባ ለመቃወም በቀይ ቀለም የታጠበ  የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶች ስም የተፃፈበት ልብስ በመልበስ ጉዳዪ በእንዲህ አይነቱ መድረክ ላይ የበልጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርገው ታይተዋል።  

የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጇ  ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ) ከዚህ ምስል ጋር በተያያዘ  ዛሬ እረፋዱን የእስር ማዘዣ ወጥቶባታል ተብሎዋል።

የአዲስ አበበአ ሊፓሊስ ህዝብ ግንኙነት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን በስልክ አነጋግሪ ነበር እሳቸውም የአዲስ አበአባ ፖሊስ በጉዳዪ ላይ የሚያውቀው ነገር የለም በሚል ዝርዝር መረጃ  ከመስጠት ተቆጥበው ነገርግን  ፖሊስ በቁጥጥሩ ስር ያዋላቸውን ግለሰቦች በ 48 ሰአት ወስጥ ፍርድቤት የመቅረብ ግዴታ አልበት ሲሉ ተናግረዋል ። የፊዲራል ፖሊስ ለማነጋገር ያደረግሁት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም።

ሐና ደምሴ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር