1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስለ ጋዜጠኞች እስራት

ሐሙስ፣ ግንቦት 25 2014

የጋዜጠኞች በጅምላ መታሰር በቅርቡ ተበራክቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ብቻ ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች መኖራቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ያሳስበናል ብሏል።

https://p.dw.com/p/4CC7s
Karte Äthiopien englisch

ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል

የጋዜጠኞች በጅምላ መታሰር በቅርቡ ተበራክቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ብቻ ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች መኖራቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ያሳስበናል ብሏል። ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነውም ብሎዋል።

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እየተበራከተ የመጣው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን፣ መግለጫ አውጥተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን 18 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። መንግስት በቁጥጥር ስር ያረደጋቸው ጋዜጠኞች አንዳንዶቹ  ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው ምክር ቤቱን አሳስቦታል ብለዋል ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው፤ ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ  መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነው ተብሎዋል።  ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከመገናኛ ብዙኃን ሥራቸው ጋር በተያያዘ ከሆነ ክሱም ሊቀርብባቸው የሚገባው በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሠረት መሆን ይኖርበታል ብለዋል አቶ ታምራት ኃይሉ። የኢትዪጵያ መገናኛ  ብዙኃን ሥራ አስፈፃሚ በየግዜው የሚታየው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት የሕግ ከለላ አለማግኘት በሀገራችን ሀሳብን በነፃነት የመገፅ መብትን ጥያቂ ውስጥ ከመክተቱም ባሻገር  በሞያው ላይ ያሳደረውን ተፀኖ ክረፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።            

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ