1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሚዲያ ነፃነትና የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጥሪ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2016

ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከፍርሃት እና ጫና ነፃ ሆነው ሊሰሩ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የበሕል ድርጅት(UNESCO) ጋር በመሆን "ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ" በሚል ሀሳብ የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀንን ዛሬ አክብረዋል።

https://p.dw.com/p/4fhlc
ኢትዮጵያ: ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ
ኢትዮጵያ: ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥምስል Solomon Much/DW

የሚዲያ ነፃነትና የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጥሪ

ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከፍርሃት እና ጫና ነፃ ሆነው ሊሰሩ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የበሕል ድርጅት(UNESCO) ጋር በመሆን "ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ" በሚል ሀሳብ የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀንን ዛሬ አክብረዋል።

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኝነት ሥራ ነፃነት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል።  

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የጋዜጠኝነት መምህር እና የሀገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅት የሥራ ኃላፊ፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት በመንግሥት ድጋፍ ጭምር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቶ የነበረው ይህ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት በፈታኝ ነባራዊ ዐውድ ውስጥ መውደቁን ገልፀዋል። 

ስለ ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት የባለሙያ እና የመብት ድርጅት የሥራ ኃላፊ አስተያየት

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ይፋ ባደረገው የ 2024 ዓ . ም የሚዲያ ነፃነት ደረጃ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት 141ኛ ደረጃን መያዟን እና ባለፈው ዓመት ከነበረችበት 130ኛ በ11 ደረጃዎች ዝቅ ብላ መገኘቷን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤትምስል Solomon Much/DW

ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት 15 ጋዜጠኞች በእሥርላይ መሆናቸውንም ገልጿል። ዛሬ የሚዲያ ነፃነት በሚከበርበት ሁኔታ አጠቃላይ የዘርፉን የትላይነት የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህሩ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዘኃን ባለስልጣን የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ "ተራማጅ የሚባል የሚዲያ አዋጅ" እስከማውጣት የዘለቀ መልካም ጅምሮች ነበሩ ይላሉ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ህብረት ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ በበኩላቸው ዘርፉ የሚገኝበትን ሁኔታ ከመብት አንፃር ገልፀዋል። "ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየበረቱ እንደሆነ ነው" የሚያሳየው ሲሉ ዐውዱን ገልፀዋል።

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ችርጅት የእርስ በርስ እና ማንነት ተኮር ግጭቶች ለመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኞች ሥራ ፈተና ውስጥ መውደቅ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሷል። ዶክተር ጌታቸው ድንቁም ይህንን ይጋራሉ። 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤትምስል Solomon Much/DW

"ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገርልችን ውስጥ ግጭቶች በዙ ፣ ጦርነት መጣ፣ የፖለቲካ መካረሮች ነበሩ። እሱን ተከትሎ መገናኛ ብዙኃን ለፖለቲካ መሣሪያነት ዋሉ" ከአራት ዓመታት በፊት በሚዲያ ነፃነት 99 ደረጃ ላይ ተቀምጣ የነበረችው ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ግን 141ኛ ላይ ትገኛለች። 

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር