1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብአፍሪቃ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 18 2015

የ14 ዓመት ታዳጊ ሴኔት ግዛቸው ገጣሚ እና የመድረክ መነባንብ አቅራቢ ናት፡፡ ታዳጊዋ በተለይም በትላልቅ አገራዊ መድረኮች ከአገር ውስጥ እስከ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ውጪ አገሮችም በመጓዝ ከዕድሜዋ በላቁ ስራዎች አቅራቢነት ትታወቃለች፡፡

https://p.dw.com/p/4QZCc

አሁን ላይ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ሴኔት በትምህርቷም ትጉና ብርቱ ታዳጊ ናት፡፡ ትምህርቷን ከጀመረችበት ወቅት ጀምሮም ከአንደኛ ደረጃ ለቃም አታውቅም፡፡ በስራዎቿ በሳል አቀራረብ እና የመድረክ አያያዝ ብስለት የበርካቶችን እጅ በአፍ ያስጫነች ወጣት ሴኔት ግዛቸው፤ የዛሬ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ፕሮግራም እንግዳ ናት፡፡ ሴኔት በዚህም ለታዳጊዎች የህይወት መርህዋን እና ልምዷን እንዲሁም ገጠመኞቿን ልታጋራን ቀርባለች፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል

ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ