1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሩዋንዳዉ አስከፊ ታሪክ ምን እንማር?

ሐሙስ፣ ጥር 13 2013

« ይህን መጽሐፍ ለመተርጎም የተነሳሳሁት ኢትዮጵያ ዉስጥ በ 2008 ዓ.ም የዘር ጥላቻ  የመከፋፈል አደጋ ፤ የዘር ማጥፋት ስጋቶች ስለነበሩ፤ ያንን ለመከላከል ያግዛል፤ ኅብረተሰቡም ቢያነብ ያሉትን  ከፋፋይ ፖሊሲዎች ላይቀበል ይችላል የሚል ግምት ስላለኝ ነዉ።»

https://p.dw.com/p/3oFbC
Äthiopien Mezemir Girma Debre Berhan University
ምስል Mezemir Girma

ዘርን የተከተለዉ የፌደራል ሥርዓታችንን ልናፈርስ ይገባል

በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የእንጊሊዘኛ መምህር መዘምር ግርማ የተናገረዉ ነዉ። መምሕር መዘምር «Left to Tell» የተሰኘ አንዲት ወጣት ሩዋንዳዊት በበሩዋንዳዉ የዘር ፍጅት ጊዜ ቤተሰቦችዋ ሁሉ ሲያልቁ እስዋ በአንድ ጠባብ መፀዳጃ ክፍል ከጓደኞችዋ ጋር ተደብቃ ከሞት የተረፈችበትን  የ 90 ቀናት የሰቆቃ ጊዜን የምታስታዉስበት መጽሐፍ ነዉ። ሁቱትሲ በሚል ርዕስ ስያሜ ሰጥቶና ታሪኩን ተርጉሞ የዛሬ አምስት ዓመት ለአንባብያን ያበቃዉ መምህር መዘምር መጽሐፉን እንደድንገት በሚያስተምርበት በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ካገኘዉ እና ከአነበበዉ በኋላ በታሪኩ እጅግ መበማረኩ ነዉ ፤ ምናልባትም ለኛም አስተማሪ ሊሆን ይችላል ሲል በማሰብ ለመተርጎም የወሰነዉ። መጽሐፉ ተተርጉሞ ሁቱትሲ በሚል ርዕስ አንባብያን እጅ የደረሰዉ የዛሬ አምስት ዓመት ነዉ። መጽሐፉ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በኦሮምኛ በትግርኛም ተተርጉሞ ለአንባብያን መቅረቡን መምህር መዘምር ግርማ ታሪኩን ተናግሮአል።

Äthiopien Mezemir Girma Debre Berhan University
ምስል Mezemir Girma

«Left to Tell» በሚል ከሩዋንዳ የዘር ፍጅት በህይወት እንዴት እንደተረፈች በእንጊሊዘኛ እና በኪስዋሂሊ ቋንቋ የተረከችዉ የ 49 ዓመትዋ ሩዋንዳዊት መጽሐፍዋ ማለትም ታሪክዋ በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞአል። መፅሐፉ በብዙ የዓለም ቋንቋዎች የተተረጎመ መጽሐፍ መዝርዝር ስርም ተመዝግቦአል።  የ 49  ዓመትዋ ሩዋንዳዊት ኢማኬሊ ሊባጊዛ ስለመጽሐፍዋ ታሪክ ስትጠየቅ ፈጣሪ ያተረፈኝ ይህን ታሪክ ለዓለም ሕዝብ  እንዳወራ እንድመሰክር ነዉ ስትል ትናገራለች። ተርጓሚዉ መምህር መዘምር ግርማ ስለመጽሐፉ ምን ይለን ይሆን።

Äthiopien Mezemir Girma Debre Berhan University
ምስል Mezemir Girma

በተባበሩት መንግሥታት የቀድሞ የሩዋንዳ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ሁቱትሲ መጽሐፍን አንብበዉ ከተሞክሮአዋቸዉ ጋር በማያያዝ አስተያየት ሰጥተዋል። 

«በደብረብርሃን ከተማ ራስ አበበ አረጋይ የሚባል ቤተ-መጽሐፍት ከከፈተ አምስት ዓመት የሆነዉ የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የእንጊሊዘኛ መምህርና የሁቱትሲ መጽሐፍ ተርጓሚ መምህር መዘምር ግርማ፤ በቤተ መጽሐፍቱ ወጣቶች መጽሐፍትን እንዲያነቡ ለማነቃት አስቦ ቤተ መጻሕፍት እንዳቋቋመም ይታወቃል።  መጽሐፉን ለመሸጥ ችግር ስለገጠመዉ የመጽሐፍ ሽያጭን በራሱ መጽሐፍ መጀመሩንም ነግሮናል።  ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን  መጻሕፍት ሲጠይቁት በፖስታ ቤት በፍጥነት ያደርሳልም።   

Äthiopien Mezemir Girma Debre Berhan University
ምስል Mezemir Girma

በደብረብርሃን ዮንቨርስቲ የኢንጊሊዘኛ ሥነ-ጽሑፍ መምህር መዘምር ግርማ የተለያዩ አጫጭር የኢንጊሊዘኛ ድርሰቶችን የሕጻናት የተረት መጽሐፎችን ከእንጊሊዘኛ ወደ አማርኛ ተርጉሞአል፤ የአፍሪካ የተረት መጻሕፍት መረሃ-ግብር ላይ የሚገኙ በርካታ አጫጭር ታሪኮችንም ተርጉሞአል። መምህር መዘምር ግርማ ለሰጠን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉ ቅንብሩን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ