1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያኑ በበርሊናለ የፊልም መድረክ

ሐሙስ፣ የካቲት 19 2012

በጀርመን መዲና በርሊን ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በመዘጋጀት ላይ ባለዉ የፊልም ፊስቲቫል «በርሊናለ»  ዘንድሮ ለ 340 በላይ ፊልሞች መድረኩን ከፍቶአል። በዚህ መድረክ 18 ቱ ፊልሞች የወርቅና የብር ድቡን አሸንፎ ለመዉሰድ ዉድድር ገጥመዋል።

https://p.dw.com/p/3YXwD
BG 0 | Berlin | Berlinale Guide für Anfänger
ምስል DW/J. Yan

ኢትዮጵያውያን በበርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል

« አበሻ ቪዉ የኢትዮጵያን ፊልሞች ዉጭ ሃገር እየወሰደ የሚያስተዋዉቅ እንዲሁም ራሱን ችሎ የኢትዮጵያዉያን ፊልሞችን  ዜናዎችን ባለዉ አካል በማቅረብ ለዉችዉ ዓለም የሚያስተዋዉቅ መሥርያ ቤት ነዉ ። »   ይላሉ በበርሊን መዲና በየዓመቱ በሚካሄደዉ የፊልም ፊስቲቫል «በርሊናለ » ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዊት። 
በጀርመን መዲና በርሊን ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በመዘጋጀት ላይ ባለዉ የፊልም ፊስቲቫል «በርሊናለ»  ዘንድሮ ለ 340 በላይ ፊልሞች መድረኩን ከፍቶአል። በዚህ መድረክ 18 ቱ ፊልሞች የወርቅና የብር ድቡን አሸንፎ ለመዉሰድ ዉድድር ገጥመዋል። የአንደኛ እና ሁለተኛዉን ደረጃ እንደተለመደዉ የትላቅ የፊልም ኢንዱስትሪ ሃገራት ተሻምተዉ ይወስዳሉ ተብሎ ከወዲሁ ተገምቶአል። በፊልም ኢንዱስትሪ ጎዳ ላይ በመንገዳገድ ላይ ያለችዉ ኢትዮጵያም አንዳንድ ባለሞያዎችዋን ወደ በርሊኑ ዓለም አቀፍ መድረክ ልካለች። የበርሊኑ ወኪላችን ወደ እዚሁ መድረክ ከመጡ ኢትዮጵያዉያን  የፊልም ሥራ ባለሞያዎች መካከል ሲልቪያ ሳልዚኒ እና የአበሻ ቪዉ ስራ አስክያጅ የሆኑት ትዕግስት ከበደን አነጋግሮዋቸዋል። ይህ መሰናዶአችን የጀርመኑን ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ «በርሊናለ» ን እና በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ኢትዮጵያዉያንን ሥራ ያስቃኘናል። ሙሉ ጥንቅሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 

 

ይልማ ኃይለሚካኤል

 

አዜብ ታደሰ