1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የቀጠለው የመናገር ነጻነት ዓፈና

እሑድ፣ መስከረም 20 2016

ባለፉት ዓመታት በትግራይ የነበረውንና እየቀጠለ ያለውን ሀሳብን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለጽ ነጻነትን ጨምሮ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ዓፈና አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ፓለቲከኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይወቅሳሉ።

https://p.dw.com/p/4X0yJ
የመቐለ ከተማ በከፊል
የመቐለ ከተማ በከፊልምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

በትግራይ የቀጠለው የመናገር ነጻነት ዓፈና

 

በአለፈው ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ በተቃዋሚዎች የተጠራውን ሰልፍ ለመበተን የክልሉ የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱትን ጨካኝ የተባለው የአፈና ድርጊትን ተከትሎ የትግራይ የፍትህ ቢሮ ድርጊቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል። ሰሚ ባያገኝም። አለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጓች ድርጅት (CPJ) ባወጣው መግለጫም ድርጊቱን ሲዘግቡ በነበሩት የሃገር ውስጥና የውጭ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እንግልትና ወከባ እንዲሁም ስራቸውን እንዳያከናውኑ በጸጥታ ሃይሎች ዕንቅፋት እንደተፈጸመባቸው በመግለጽ የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል። ሰሚ ባይገኝም።
 
ሦስት የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የባይቶና አመራሮች በሰጡት መግለጫም በትግራይ ያለው የፖለቲካ ምህዳር ይበልጥ እየጠበበ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ወደማይቻልበት ሁኔታእያመራ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
 
በአጠቃላይ  ባለፉት  ዓመታት  በትግራይ የነበረውንና እየቀጠለ ያለው ሀሳብን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለጽ ነጻነትን ጨምሮ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት  ዓፈና አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ፓለቲከኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይወቅሳሉ። 

በዛሬው የእንወያይ ዝግጅት "በትግራይ የቀጠለው የመናገር ነጻነት ዓፈናና ይህን ለማሻሻል መደረግ ያለባቸው ነጥቦች" በተመለከተ የተካሄደውን ውይይት እንድትከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን። 

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር